
ወልድያ:ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁም ሁሉም ለሰላም ” በሚል መሪ መልዕክት ከወልድያ ከተማ የሃይማኖት አባቶች ጋር የውውይት መድረክ ተካሂዷል።
ለሀገር ሰላም መጸለይ ከሃይማኖት አባቶች እንደሚጠበቅም ተወያዮቹ አንስተዋል። ከቤት የወጡ ልጆችንም መምከር እና መገሰጽ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ሁሉም የሃይማኖት አስተምህሮ ሰላምን ይሰብካል ያሉት የሃይማኖት አባቶቹ በየሃይማኖት ተቋማት ለአማኙ ስለ ሰላም መስበክን እንደማያቋርጡ ነው የገለጹት።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ምሥራቅ እዝ ምክትል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንደ ሀገር የጠፋውን የመከባበር እና የመደማመጥ እሴት መመለስ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት በተሰማራበት ቀጣና ሰላምን ለማስፈን 24 ስዓት ይሠራል ነው ያሉት። ኢትዮጵያን በዘር እና በሃይማኖት ከፋፍለው ለመበታተን የሚሠሩትን የውስጥ እና የውጭ ኀይሎችን ማውገዝ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የሃይማኖት ተቋማትም ከእንደዚህ አይነት ያልተገባ ተግባር ሊርቁ እንደሚገባም ገልጸዋል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ11ኛ እዝ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አድማሱ ዓለሙ መከላከያ ሠራዊት ለሕዝብ ሰላም ይሠራል ብለዋል። የሃይማኖት አባቶችም ሰላምን ለማስፈን የራሳቸው አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ነው የተናገሩት።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ የሃይማኖት አባቶች እውነተኛ የሃይማኖት አባት እና መልካም ልጅ የሚያወጡ መኾን እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!