
ባሕር ዳር:12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እፈጻጸም ግምገማ እና በቀጣይ አቅጣጫ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን፣ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር፣ የሰሜን ጎጃም እና የደቡብ ጎንደር ዞኖች የትምህርት ባለድርሻ አካላት በውይይቱ እየተሳተፉ ነው።
በውይይቱ ላይ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ ( ዶ.ር) ቀጣይነት ያለው የሀገር ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ቴክኖሎጅን የሚያላምድ ብሎም የሚያመነጭ ትውልድ ለመፍጠር ትምህርት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል።
ይሁን እንጅ ባለፉት ዓመታት የትምህርት ሥርዓት ለሥነ ምግባር እና ለሀገር በቀል እሴቶች ትኩረት ከመስጠት ይልቅ በውጭ የትምህርት ሥርዓት ላይ የተንጠለጠ መኾኑ አንዱ ችግር እንደነበር ነው የገለጹት።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በጸጥታ እና ሌሎች ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሥርዓቱ እየተፈተነ መኾኑን አንስተዋል።
በርካታ ተማሪዎችም ከትምህርት ገበታ ውጭ መኾናቸውን አንስተዋል። በዚህ ዓመትም 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መኾናቸውን አንስተዋል።
በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን