
አዲስ አበባ: ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በቻይና የሻንሺ ግዛት እና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ኮንፈረንስ ተካሂዷል
በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የንግድ ሚኒስትር ድኤታ እንዳለው መኮንን የቻይና ሻንሺ ግዛት በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራ እና በአምራች ዘርፉ ያላትን አቅም ከኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብት እና የሰው ኀይል ጋር አቀናጅቶ ለጋራ ብልጽግና መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የሻንሺ ግዛት ምክትል አሥተዳዳሪ ዋንግ ዢያዎ ባለፈው ዓመት ብቻ የኢትዮጵያ እና የግዛቷ የንግድ ልውውጥ በ9 በመቶ ማደጉን ገልጸዋል።
ግዛቷ ከ120 በላይ ዩኒቨርሲቲ እና ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ያሏት ከመኾኗም በተጨማሪ በቻይና ሥልጣኔ እና ምርምር ቀዳሚ እንደኾነችም አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ፈጣን ኢኮኖሚ ያላት ሀገር በመኾኗ በግብርና፣ በታዳሽ ኀይል እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በጋራ የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸውም ጠቁመዋል።
በዕለቱም የተለያዩ የቢዝነስ ለቢዝነስ ግንኙነቶች እና የትብብር ፊርማዎች ተካሂደዋል።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!