
ባሕር ዳር: ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በባሌ ዞን በነበረን የሁለተኛ ቀን ቆይታ የወልመል ወንዝ የመስኖ ልማት እና ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ጉብኝት ባሻገር ወደ ባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሀረና ክላስተር በመገኘት ምልከታ አድርገናል ብለዋል።
እነዚህ በግንባታ ላይ በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ያሉ ፕሮጀክቶች በሃረና ደን የሪራ ኢኮ ሎጅ፣ ከባቢውን፣ የመመገብያ ስፍራዎችን፣ በእግር እና መኪና መንገዶች የቡና ሱቆችን፣ የምግብ አዳራሾችን እስከ ቱሉ ዲምቱ የከፍታ መወጣጫ ስፍራዎች የሚያካትቱ ናቸው ነው ያሉት።
እነዚህ የልማት ሥራዎች ዘላቂ የቱሪዝም ፕሮጀክቶች የአካባቢ የሥራ ፈጠራ ዕድልን የሚያሰፉ እና የጎብኝዎችን ዕድል የሚያሰፉ በመኾኑ በልዩ ምልከታ የሚታዩ ናቸው ብለዋል በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!