
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 18ኛውን የሠንደቅ ዓላማ ቀንን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጲያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ” በሚል መሪ መልዕክት እያከበረ ነው።
የሠንደቅ ዓላማ ቀን አከባበሩ በተለያዩ ሁነቶች የታጀበ ነው። በበዓሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ የክልሉ ፖሊስ ማርሽ ባንድ እና የአድማ መከላከል ፖሊስ አባላት የተለያዩ የሰልፍ ትርዒቶችን እያሳዩ ነው።
በክብረ በዓሉ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አማረ ሰጤ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይም፦
👉ሠንደቅ ዓላማችን የጀግንነታችን እና የአይበገሬነታችን መገለጫ፣ የነጻነታችን ማማ፤
👉ሠንደቅ ዓላማችን የሕዳሴያችን ሕያው ምስክር፣ የሉዓላዊነታችን መገለጫ፣ የሀገራችን ታላቅነት ማብሰሪያ ነው።
👉ሠንደቅ ዓላማችን የዘመናት የነጻነታችን እና የሥልጣኔያችን አብሪ ኮከብ ምልክት ነው የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!