
ባሕር ዳር: መስከረም 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡ የሞዴል የገጠር መንደሮች አስረክበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ረቡዕ በሀላባ እና ከምባታ ዞኖች የነበረንን የሞዴል የገጠር መንደሮች ርክክብ ሥነ ሥርዓት በመቀጠል ዛሬ ደግሞ በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡትን አስረክበናል ብለዋል።
እነኚህ ባለሦሥት መኝታ ቤት መኖሪያዎች ለማብሰል የሚያገለግል የባዮጋዝ መሣሪያ፣ የፀኃይ ኃይል ማመንጫ፣ የዶሮ ማርቢያ፣ የተለየ የእንስሳት በረት የተሟላላቸው ናቸው። በተመጣጣኝ አነስተኛ ወጪ ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች የተሻለ መኖሪያ ከማስገኘት አንፃር ለገጠሩ ማኅበረሰብ ብልጽግና ያለንን ሕልም የሚያሳይ ነው።
እንደ ማኅበረሰብ አዲስ ሀሳቦች ሲፈልቁ “አይቻልም” በሚለው የቆየ አስተሳሰብ የመፈተን ተግዳሮት ይደቀንብን ይሆናል። ይሁንና በተጨባጭ በሚታየውና በተገኘ ውጤት ላይ ወደ አለማመን እና አለመቀበል በሚመራን የሀሳብ ወጥመድ ውስጥ መውደቅ የለብንም ነው ያሉት።
ዜጎች ለውጥ እንደሚቻል ሀብቶቻችንን ወደ ትክክለኛ የቅድሚያ ትኩረቶቻችን ካዋልንም ማኅበረሰብን በርግጥም ማሻገር እንደምንችል ማመን ይገባቸዋል። በአራቱ ዞኖች የተሠራው ሥራ በመላው ክልሉ መደገም ይኖርበታል። የክልሉ መሪዎች ይኽን ታላቅ ሥራ እንደሚፈጽመውም እምነት ጥያለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!