
ባሕር ዳር: መስከረም 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች ለኾኑ ሕጻናት የሚሰጠው የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በሰላም አድርጊው ማርያም ቤተ ክርስቲያን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች፣ የጤና ተቋም መሪዎች እና ጤና ላይ የሚሠሩ ረጅ ድርጅት ኀላፊዎች ተገኝተዋል።በዕለቱ የሃይማኖት አባቶች ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!