
ባሕር ዳር: መስከረም 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ትናንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት ሰባተኛው ታማኝ ግብር ከፋዮች የዕውቅና ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
በ2010 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው ይኽ ሥነ ሥርዓት የዜግነት የግብር ግዴታቸውን በወቅቱ እና በታማኝነት የሚፈፅሙ ዜጎችን ለማበረታታት ታቅዶ የሚተገበር ነው።
በዘንድሮው መርሐ ግብር 700 ታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል። በ2017 ዓ.ም እንደነበራቸው አስተዋጽኦ መጠን 105 የፕላቲኒየም ደረጃ፣ 245 የወርቅ ደረጃ፣ 350 ደግሞ የብር ደረጃ ተሸላሚ ኾነዋል ተብሏል።
የጋራ አስተዋጽኦዋቸው በሥራ ዘመኑ 900 ነጥብ 22 ቢሊዮን ብር በግብር እንዲሰበሰብ አስችሏል ነው የተባለው።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በግብር እና ቀረጥ አሰባሰብን ብቁ እና ግልፅ የሚያደርጉ የዲጂታል ሥርዓቶችን አስጀምረዋል። ከነዚህም ውስጥ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት፣ ኤሌክትሮኒክ የጉምሩክ አሥተዳደር ሥርዓት እና ኤሌክትሮኒክ የጭነት መከታተያ ሥርዓት ይገኙበታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!