የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት

24
የPulse of Africa ሚዲያ ሥራ መጀመር አፍሪካን በአሉታዊ ገጽታ የማቅረብ ሥራን ለመመከት ብሎም የራሳችንን ትርክት በራሳችን የመቅረጽ ተግባራችንን የምናፀናበት ጠቃሚ ርምጃ ነው። ምንም እንኳ አፍሪካ ሰፊ እና እምቅ ሀብት ያላት አኅጉር ብትሆንም አብዛኛውን ጊዜ እንደ አነስተኛ እና አቅመቢስ ተደርጋ ትሳላለች።
በዚህ የተነሳ ነው አነስተኛ ግን እጅግ ትርጉም ያለው የPulse of Africa ጅማሮ በመጪዎቹ ጊዜያት ከፍ ወዳለ መሪ አኅጉራዊ ሚዲያ የማደግ መንገድ እጅግ ጠቃሚ የሚሆነው።
አፍሪካ ዐቢይ የኢንደስትሪ ማዕከል እና የአለም ቁልፍ ሚና ተጫዋች የመሆን መንገድ ላይ በማያጠራጥር መንገድ እየተጓዘች ትገኛለች። የPulse of Africa መቋቋም ወደፊት የመመልከት ርምጃ ነው። በአለም መድረክ ጠንካራ እና ቱባ የአፍሪካ ድምፅ የማሰማት መሠረትም ነው።
Previous articleችሎት ላይ ያለን ሥነ ሥርዓት ምን ያህል ያውቃሉ?