
ባሕር ዳር፡ መስከረም 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለዚህም መንግሥት ምርትን በብዛት፣ በጥራት እና በአይነት እንደሚያሳድግም አብራርተዋል።
የውጭ ንግድ የማሳደግ ሥራ በመሥራት ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማምጣት እንደሚሠራም አስረድተዋል። የግሉን ዘርፍ የሚያሳድጉ፣ ቁጠባን የሚያበረታቱ እና ኢንቨስትመንትን የሚያልቁ ሥራዎች እንደሚሠሩም ነው ያስገነዘቡት።
ሀገሪቱ ከድህነት ወጥታ ራሷን ቀና የምታደርግበት ሥራ እንደሚሠራም ነው የተናገሩት። መንግሥት በውጭ ላይ ተጽዕኖ ሸብረክ የማይል እና በራሱ የሚቆም ኢኮኖሚ ለመገንባት እንደሚተጋም ጠቁመዋል።
መንግሥት ባለፉት ዓመታት የዋጋ ግሽበትን ሊቀንሱ የሚያስችሉ ሥራዎችን በመሥራት ጉልህ ጥረት ማድረጉንም አስገንዝበዋል። በዚህ ዓመትም ጥረቱ ተጠናክሮ የዋጋ ግሽበቱን ወደ ነጠላ አሐዝ እንዲወርድ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
ምርትን በማሳደግ አቅርቦትን በማሻሻል የግብይት ሥርዓቱን በማዘመን በከተማ ግብርና፣ በስንዴ ልማት እና በሌማት ትሩፋት የተገኙ ውጤቶችን በማስጠበቅ የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል እንደሚሠራም አስረድተዋል።
ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠርም የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባሩ እንደኾነ ነው የጠቆሙት። በሴፍትኔት የሚተዳደሩ ዜጎች ወደ ምርታማነት እንዲሸጋገሩ እንደሚደረግም ተናግረዋል።
ለሥራ ዕድል አቅም ያላቸውን ዘርፎችን በመለየት በውጭም ኾነ በሀገር ውስጥ በርከት ላሉ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሠራም ጠቁመዋል።
ግብርናው በዚህ ዓመት የ6 ነጥብ 8 በመቶ ዕድገት እንዲያስመዘግብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራልም ብለዋል። የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ይሠራልም ነው ያሉት።
የመስኖ ተግባርን በማጠናከር ግብርናው ከዝናብ ጥገኝነት የሚላቀቅበትን አሠራር በመፍጠር እና ግብዓትን በሀገር ውስጥ በማምረት በተለይም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በዚህ ዓመት ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች እንደኾኑም ነው የተናገሩት።
ፈጣን የኢንዱስትሪ ልማት ለማረጋገጥም እንደሚሠራ ነው ያስረዱት። የግሉ ዘርፍም በኢንዱስትሪው ዘርፉ የጎላ ተሳትፎ እንዲኖረው እንደሚሠራም ጠቁመዋል።
በዚህ ዓመት ከፍተኛ በጀት ለሚጠይቁ አምራች ኢንዱስትሪዎች ትኩረት እንደሚሰጠውም ነው ያብራሩት። ለኢንዱስትሪ ፓርኮችም ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራም አብራርተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን