
ባሕር ዳር፡ መስከረም 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ3ተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ለመስጠት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ በክልሉ በአንዳንድ አካባቢዎች የፖሊዮ በሽታ ተከስቷል ብለዋል።
በሽታውን ለመከላከል በዘመቻ መልክ ክትባቱን መስጠት አስፈላጊ መኾኑ ታምኖበታል ነው ያሉት።
ወረርሽኙ በተከሰተባቸው እና በሽታው ባልተከሰተባቸው ዞኖች እና ከተማ አሥተዳደሮች ክትባቱ ይሰጣል ብለዋል።
በክትባት ዘመቻው በክልሉ ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች የኾኑ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ተደራሽ እንደሚኾኑም ገልጸዋል።
የክትባት ዘመቻውን ውጤታማ ለማድረግ እና ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀልበስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች ለክትባቱ ተደራሽነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!