
ባሕርዳር ፡መስከረም 25/2018ዓ.ም (አሚኮ) “በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል” በሁለንተናዊ የለውጥ ሂደቶች ውስጥ ያለው የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሪ መልዕክት ነው።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጀመረውን የሪፎርም ሥራ ዲጂታላይዜሽን ማብሰሪያ እና የአዲስ ሕንጻ ምረቃ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።
በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና የሕዝብን ደኅንነት ለመጠበቅ በሙያ ብቃቱ የላቀ፣ በጀግንነት የሚሠራ እና በሰብዓዊነት የሚያገለግል የፖሊስ ተቋም ለመገንባት የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች ሲሠሩ ቆይተዋል።
የሪፎርም ሥራዎቹ ሕዝባዊ መሠረት ያለው የፖሊስ ሠራዊት ለመገንባት የሚያስችሉ፣ ዘመኑን የዋጁ አደረጃጀቶችን ለመፍጠር ያለሙ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የሚያስታጥቁ ናቸው።
በዛሬው የሪፎርም ሥራዎች ዲጂታላይዜሽን ማብሰሪያ እና የአዲስ ሕንጻ ምረቃ መርሐ ግብር ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የፌደራል እና ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!