ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሪፎርም ሥራ፣ የዲጂታላይዜሽን ማብሰሪያ እና አዲስ ሕንፃን ይመርቃሉ።

17
ባሕርዳር ፡መስከረም 25/2018ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሪፎርም ሥራ፣ የዲጂታላይዜሽን ማብሰሪያና አዲስ ሕንፃን ለመመረቅ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ባሕርዳር ገብተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ተፈጥሮ በውኃ፣ በልምላሜ እና በዘንባባ በኳላት ውብ ምድር ባሕርዳር ገብተናል ብለዋል።
በቆይታችን የአማራ ክልል ፖሊስ የሪፎርም ሥራ፣ የዲጂታላይዜሽን ማብሰሪያ እና አዲስ ሕንፃን እናስመርቃለን ነው ያሉት።
በተጨማሪም በፈጠራ እና ፍጥነት እሳቤ በተቃኘ ልማት ላይ የምትገኘውን ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ተዘዋውረን እንመለከታለን ብለዋል።
በባሕርዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሞቀ አቀባበል ላደረጉት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ ለካቢኒያቸው እና ለባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር መሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየሦስት ሊቃውንት የአሻራ ቅብብሎሽ
Next articleበጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል