የአፈር አሲዳማነትን በመከላከል ምርታማነትን ለመጨመር እየተሠራ ነው።

2
ባሕር ዳር፡ መስከረም ፡ 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዴት ግብርና ማዕከል ምርት እና ምርታማነትን ለመጨመር ማነቆ የኾነውን የአፈር አሲዳማነት ለመከላከል እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል።
የአዴት ግብርና ማዕከል በባሕር ዳር ከተማ የበቆሎ ሰብልን በአሲዳማ መሬት ላይ ለመሞከር እየሠራ ያለው ሥራ አስጎብኝቷል።
የአዴት ግብርና ማዕከል ዳይሬክተር አታክልት አበበ
የኦስፒ ኢትዮጵያ ማዳበሪያን በመጠቀም የጤፍ እና የበቆሎ ሰብልን በአሲዳማ መሬት ላይ ተግባራዊ እያደረገ መኾኑን ገልጸዋል። ሥራው ውጤት እየተገኘበት መኾኑንም ተናግረዋል።
የኦስፒ ኢትዮጵያ የአፈር ማዳበሪያ በአሲዳማ መሬት ላይ ምርት እንዲመርት ከማድረግ በተጨማሪ አሁን እየገጠመ ያለውን የማዳበሪያ መግዥ ወጭ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ያስችላል ብለዋል።
በቀጣይ ለአርሶ አደሮች እንዲሰራጭ ለማድረግ ተከታታይነት ያለው ሥራ እንደሚሠራ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ሊታረስ ከሚችለው መሬት መካከል 42 በመቶ የሚጠጋው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ መኾኑን የተናገሩት በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንት እና ግብዓት ዘርፍ የሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ደረጀ አሳምነው ናቸው። የአዴት ግብርና ማዕከል የኦስፒ ኢትዮጵያን ማዳበሪያ ተጠቅሞ ያለማው የሰብል ውጤት የታየበት ነው ብለዋል።
በአፈር ለምነት ላይ የሚያጋጥመው አሲዳማነትን በመቀነስ ምርት እና ምርታማነትን ለመጨመር እንደ ሀገር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።
በአዴት ግብርና ማዕከል እየተሠራ ያለውን ተግባር ወደ አርሶ አደሮች ለማስፋት መሠራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ሰመሀል ፍስሀ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየውኃ ጉድፍ በሽታ ምንድን ነው?
Next articleተቋማት ግልጸኝነት እና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተሠራ ነው።