የምክር ቤቶቹ የጋራ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት መስከረም 26/2018ዓ.ም ይካሄዳል።

7
ባሕር ዳር፡ መስከረም 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ)6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ሰኞ መስከረም 26 /2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት መሠረት የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰባ እንደሚከፍቱ ተገልጿል፡፡
የ6ኛው ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትም የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
በተገኙበት ሰኞ መስከረም 26/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል ተብሏል።
በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌደራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ፡፡
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በምክር ቤቶቹ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአረጋውያን አስታራቂ ናቸው።
Next article“ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ የሚጠቀሙ ማንኛውም ከባድ ተሽከርካሪዎች (ትራክ) ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት የተከለከለ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)