ጤና ሚኒስቴር ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚቆየውን ሁለተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጤና ደህንነት ትግበራ ይፋ አደረገ።

5
አዲስ አበባ: መስከረም 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ይህ የጤና ደህንነት ከዓለም አቀፉ የጤና ደንብ ጋር ተጣጥሞ የሚተገበር እንደኾነ የተናገሩት የጤና ሚኒስትሯ መቅደስ ዳባ (ዶ.ር) ናቸው። በዋናነትም በጤናው ዘርፍ፣ በግብርናው ዘርፍ እና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ተቀናጅቶ የሚተገበር እንደኾነም ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ ትግበራው ሦስት ሁነቶች ላይ የተለየ ትኩረት ማድረጉን ገልጸዋል። እነዚህም ብሔራዊ ፍላጎትን ከጤና ጋር አቀናጅቶ በመተግበር ጤናማ አካባቢን መፍጠር፣ የብሔራዊ አደጋ እና ምላሽን ማሳደግ እንዲሁም ማቀናጀት እና የአንድ ጤና ማዕቀፍ ሥራን ማጠናከር መኾናቸውን አብራርተዋል።
በዚህ የትግበራ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ የተለያዩ አጋራ ተቋማት እና የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየአማራ ክልል መንግሥት ሙስናን ለመታገል ቁርጠኛ አቋም ይዟል።
Next articleየአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ በጀትን አጸደቀ።