በአማራ ክልል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት እና የዕውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

27
ባሕር ዳር: መስከረም 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት እና የዕውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። በመርሐ ግብሩ ከ500 ነጥብ በላይ ያመጡ 452 ተማሪዎች ይሸለማሉ ተብሏል።
ዘጋቢ:- ዋሴ ባዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያከናወናቸው የለውጥ ሥራዎች ለተገልጋዩ ኅብረተሰብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለቸው በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው” ፍፁም አሰፋ (ዶ.ር)
Next articleሰላምን የሚነሱ ተልዕኮ ተሸካሚ የውስጥ ተላላኪዎችን በኅብረት መታገል ያስፈጋል።