“ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያከናወናቸው የለውጥ ሥራዎች ለተገልጋዩ ኅብረተሰብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለቸው በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው” ፍፁም አሰፋ (ዶ.ር)

7
ባሕር ዳር: መስከረም 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ.ር) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያከናወናቸውን የለውጥ ሥራዎች ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጡን ግልፅ፣ ወጭ ቆጣቢ፣ ተደራሽ እና ውጤታማ ለማድረግ የሠራቸውን ምቹ ችሎቶች፣ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች፣ ሕፃናት ይዘው የሚመጡና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የተገልጋዮች ማረፊያ፣ የሠራተኞች የህፃናት ማቆያ እና የፍትሕ ሙዚየምን ጉብኝት አድርገዋል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው በ2017 ዓ.ም ስለተከናወኑ እና በ2018 ዓ.ም ስለታቀዱ የለውጥ ሥራዎች ዝርዝር ገለፃ አድርገውላቸዋል።
ሚኒስትሯ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በአጭር ጊዜ ያከናወናቸው የለውጥ ሥራዎች ለተገልጋዩ ኅብረተሰብ ከፍተኛ ፋይዳ ያለቸውና ለሌሎችም በተሞክሮነት ሊወሰድ የሚገባው ተምሳሌት የሆነ ሥራ እንደሆነ ገልጸዋል። በጉብኝቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሃመድ (ዶ.ር) እና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አልማዝ መሰለ ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የቀይ ባሕር ባለቤቶች”
Next articleበአማራ ክልል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት እና የዕውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።