
“እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የሚከተለውን የበዓል መልዕክት አስተላልፈዋል፦
የመስቀል በዓል እንደገና የመገለጥ እና እንደገና የማንሣት በዓል ነው። መስቀሉ ከ300 ዓመታት በላይ ተቀብሮ ነበር። የጠፋና የተረሳ፤ ያለቀና የደቀቀ መስሎ ነበር።
ከዘመናት በኋላ ግን ብርቱ መሪ ሲያገኝ ደመራው ተደምሮ፣ ተራራው ተቆፍሮ እንደገና ወጣ። እንደገና ተገለጠ።
ይህ ለኢትዮጵያም የሚሠራ ነው። እንደገና ትነሣለች፣ እንደገና ታበራለች። እንደገናም ለዓለም ትገለጣለች።
መልካም የደመራ እና የመስቀል በዓል ይሁንልን።