
ባሕር ዳር፡ መስከረም 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በባሕርዳር ከተማ ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) እና ሌሎች ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል። በመድረኩ አሁናዊ የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ እየተገመገመ ነው።
በደቡብ ጎንደር እና በጎጃም ቀጣና ያለው የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ በርካታ ለውጦች የታዩበት እንደኾነ በዕለቱ ተነስቷል። ሰላምን ዘላቂ እና አስተማማኝ ለማድረግ በቀጣይ የሚከናወኑ ቁልፍ ሥራዎች ላይ መግባባት መደረሱም ተመላክቷል።ከባሕርዳር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በቀጣይ ጊዜያት የክልሉን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ ማኅበረሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እና በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት ሥራዎች እንዲዞር ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!