“ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ አጠቃላይ ውይይት አካሂደናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

11
ባሕር ዳር፡ መስከረም 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ አጠቃላይ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።እነዚህም የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን ያካትታሉ። በተለይም ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁሕ ኃይል ለማቅረብ የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ለማልማት ስምምነቶችን በመፈራረም የጋራ ፍላጎቶቻችንን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ተመካክረናል ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበመስቀሉ ይቅር እንደተባልን እኛም እንዲሁ ይቅር እንባባል።
Next articleየመስቀል በዓል ለማኅበረሰቡ አብሮነት እና የእሴት ግንባታ ፋይዳው ከፍ ያለ ነው።