ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ይፋ አድርጓል።

33
ባሕር ዳር: መስከረም 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በባሕር ዳር ከተማ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚኾኑ መንገዶችን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ይፋ አድርጓል፡፡
በመኾኑም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁት መንገዶች ዝግ መኾናቸውን ተገንዝበው ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
በዚሁ መሠረት ከቀኑ 7፡ 00 ሰዓት ጀምሮ እስከ በዓሉ ፍፃሜ ድረስ፡-
👉 ከሳፍሪ ሞል እስከ አመዶ ገበያ
👉 ከድሮው ጊዮን ሆቴል ወይም ትራፊክ መብራት እስከ አዝዋ ሆቴል
👉 ከፋሲሎ ትምህርት ቤት እስከ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት
👉 ከዲላኖ ሆቴል እስከ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ውስጥ ለውስጥ ያሉ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ይኾናሉ።
ኅብረተሰቡም ከፖሊስ የሚሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ጥሪ ማቅረቡን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article” በመስቀል ብርሃን ወደ ሰላም ልንሸጋገር ይገባል” ብጹዕ አቡነ ዘካርያስ
Next articleጊዜያዊ የረዥም ጊዜ (የኮንትራት) ቅጥር ማስታወቂያ