በሰላም እና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሄደ።

21
ደሴ: መስከረም 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሂዷል።
መድረኩ አሁናዊ የሰላም እና የጸጥታ ሁኔታን የሚገመገምበት እንደኾነ ተገልጿል።
በወሎ ቀጣና ያለው የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ በርካታ ለውጦች የታዩበት እንደኾነ በዕለቱ ተነስቷል። ሰላሙን ዘላቂ እና አስተማማኝ ለማድረግ በቀጣይ የሚከናወኑ ቁልፍ ሥራዎች ላይ መግባባት መደረሱም ተመላክቷል።በቀጣይ ጊዜያት የክልሉን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ ማኅበረሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እና በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት ሥራዎች እንዲዞር ሰላሙን አስተማማኝ ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።
በውይይት መድረኩ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ.ር)፣ የሰሜን ምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮልን ጨምሮ ሌሎች የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጄኔራል መኮንኖች፣ የዞን አሥተዳዳሪዎች እና ከንቲባዎች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የሥራ መሪዎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ:- ጀማል ይማም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየጋራ እንጅ የግል ባሕር የለም።
Next article”ዛሬ አግዘን ያስተማርናቸው ልጆች ነገ ሀገር እንዲያግዙ የቤት ሥራ እየሰጠናቸው ነው” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)