ምክር ቤቶች የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከእስካሁኑ የበለጠ መሥራት አለባቸው፡፡

4
ባሕር ዳር: መስከረም 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (ዩኤንዲፒ) ድጋፍ ለዞን፣ ለወረዳ እና ለከተማ ምክር ቤት ፎረሞች ሥልጠና እየሰጠ ነው።
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ምክር ቤቶች የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዋነኛ ዓላማቸው ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል በላፉት ጊዜያት ባጋጠመው የጸጥታ ችግር ምክንያት የቀበሌ እና የወረዳ ምክር ቤቶች ጉባኤዎቻቸውን በአግባቡ አላደረጉም ነው ያሉት። በርካቶችም ድባቴ ውስጥ ገብተው እንደቆዩ አስታውሰዋል።
ዋና አፈ ጉባኤዋ ለምክር ቤት አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሥጠት ከድባቴ ያወጣል፤ ከቁዘማ ያነቃል፤ ለላቀ ውጤታማ ሥራም ያነሳሳል ነው ያሉት።
ሥልጠና በራሱ ግብ እና ስኬት አይደለም ያሉት አፈጉባዔዋ ክፍተትን እየሞሉ አጥጋቢ ሥራ ለመሥራት ግን አጋዥ እንደኾነ ነው የጠቆሙት።
ከሥልጠናው በኋላም የሕዝብ ተወካይ የኾኑት የምክር ቤት አባላት የተሠሩ ሥራዎችን ለኀብረተሰቡ ማሳወቅ እና ለላቀ ሥራ ማነሳሳት አለባቸው ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየፍኖተ ሰላም ጤና አጠባበቅ ጣቢያን የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ተችሏል።
Next articleምክር ቤቶች ሕዝብ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲኾን መሥራት ይገባቸዋል።