ሕዳሴ በጋራ ችለናል የሚለውን የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን እና አቋማችንን በጉልህ ያሳየ ነው።

7
ባሕር ዳር: መስከረም 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በሲዳማ ክልል ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፉ በአንድነት እንችላለን፤ የሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ማንሠራራት ምልክት ነው፤ የሕዳሴ ግድባችን የብልጽግናችን ማሕተም ነው፤ የሕዳሴ ግድቡን መጨረስ የድል ሽልማት መጎናጸፍ ነው የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።
ሰልፈኞቹ መንግሥት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ እያከናወናቸው ለሚገኙ ሥራዎች ያላቸውን አድናቆት እና አጋርነት የሚገልጹ መልዕክቶችንም አስተላልፈዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ የሕዳሴ ግድባችን የኤሌክትሪክ ኃያል ማመንጫ ብቻ ሳይሆን አይቻልም የተባለውን ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደአቅሙ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል።
ሁሉም የራሱን አሻራ ያሳራፈበት የግድቡ ግንባታ መጠናቀቁ በጋራ ችለናል የሚለውን የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን እና አቋማችንን በጉልህ ያሳየ ነው ብለዋል።
‎ በቀጣይም ”በጋራ አንችላለን” በሚል እሳቤ በሕዳሴ ግድቡ ግንባታ የታየውን መነሳሳትና ቆራጥነት በተባበረ ክንድ በሌሎች ልማት ዘርፎችና በቀይ ባሕር ለመድገም እንነሳለን ነው ያሉት።
‎ከሲዳማ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በሕዳሴ ግድብ በተባበረ ክንድ ያስመዘገብነውን ድል በሌሎች ልማቶችም እንደግመዋለን ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት፦
Next articleየባሕር በር ያስፈልገናል ስንል ለቅንጦት አይደለም።