የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

6
ባሕር ዳር: መስከረም 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከተለያዩ የኢትዮጵያ ተራሮች በሸለቆ እና በሜዳ ገሰግሶ እንደሚገናኘው ታላቁ ዓባይ የብዝሃነት ቤት በሆነችው ድሬዳዋ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ የድጋፍ ሰልፍ ተደርጓል፡፡
የሕዳሴ ግድብ ከጫፍ እስከ ጫፍ በሁሉም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የኢትዮጵያ ልጆችን ለልማት ያስተባበረ፣ የመደመር ዕሳቤ የታተመበት ፕሮጀክት ነው።
በሕዳሴ ግድብ ያየናቸው በፈተናዎች መካከል እንደ አለት ጸንቶ በመቆም ማሸነፍ በደሬዳዋ ያሉ የልማት አቅሞችን ለሃገር ልማት ለማዋል ብርታት ይፈጥራል፡፡
ድሬዳዋ የሰላም እና የፍቅር ብቻ ሳይሆን ልማት እና ለለውጥ መበርታትም መገለጫዋ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሕዳሴ የመቻል ማሳያ ነው።
Next articleየሰቆጣ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።