“በዕቅድ የመመራት ልምድ ውጤታማ አድርጎኛል” ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተማሪ

3

ደብረ ብርሃን: መስከረም 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ተማሪ ሚኪያስ ኪዳኔ በደብረ ብርሃን ከተማ የኀይለማርያም ማሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው። ተማሪ ሚኪያስ በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በመውሰድ በከተማዋ ከፍተኛውን ውጤት አስመዝግቧል። 572 በማስመዝገብ በትምህርት ዘመኑ ከፍተኛ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች መካከል እንዲጠቀስም ኾኗል፡፡

ከልጅነቱ ጀምሮ ጥሩ የትምህርት አቀባበል እንደነበረው የሚናገረው ተማሪ ሚኪያስ ያለንን ዕውቀት እንዲጎለብት በውጤታማ ንባብ የታገዘ የጥናት ስልትን መጠቀም ያስፈልጋል ነው የሚለው፡፡

በጥናት ውጤታማ በሚኾንበት ሰዓት ዕቅድ በማውጣት የሚያነበው ሚኪያስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግብ እንዳገዘው አንስቷል። የሚተገበር የጥናት ዕቅድ አወጣለሁ፤ ይሄን ልምድ በትክክል መጠቀም መቻሌ ውጤታማ አድርጎኛል።

የልጆችን የትምህርት ውጤታማነት ከሚወስኑት ጉዳዮች መካከል የወላጆች ክትትል እና እገዛ የሚጠቀስ መኾኑን ይናገራል።

የተማሪ ሚኪያስ ወላጅ አባት አቶ ኪዳኔ ግዛው ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ልጃቸው የሰመረ የትምህርት ጉዞ እንዲኖረው ሲከታተሉት እንደነበር ተናግረዋል።

ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት አቀባበል መሰረት በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ የቅርብ ድጋፍ ቢያደርጉ በውጤታቸው ላይ በጎ ተጽእኖ መፍጠር እንደሚችሉ መክረዋል።

ዘጋቢ:- ገንዘብ ታደሰ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሕዳሴን ድል መርህ እና አርዓያ ያደረገ ልማት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ ይጠበቃል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next article“የተገነቡት የመሠረተ ልማት ሥራዎች ካለፉት ዓመታት በላቀ ሁኔታ የከተማዋን እንቅስቃሴ ያነቃቁ ናቸው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ