“በሶማሌ ክልል ያየነው የድጋፍ ሰልፍ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ስንቅ የሚሆን ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

10
ባሕር ዳር: መስከረም 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በሶማሌ ክልል ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል።
ሰልፉን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የስንዴ እና የሩዝ ልማት ‘አብዮት’ በሚባል ደረጃ በአጭር ጊዜ እየተስፋፋ እና እየለማበት ለሚገኘው የሶማሌ ክልል ሕዝብ የሕዳሴ መጠናቀቅ በትጋት ታሪክን መቀየር እንደሚቻል ማሳያ ሆኖለታል ብለዋል።
በሶማሌ ክልል ያለው እምቅ ፀጋ በመደመር እሳቤ ለሀገር እና ለትውልድ አሻራን ለማኖር ትልቅ አቅም መፍጠር የሚችል መኾኑን ገልጸዋል።
የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ በክልሉ ያየነው የድጋፍ ሰልፍ በርትቶ ለመሥራት፣ ልማትን ለማስቀጠል እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ስንቅ የሚሆን ነው ብለዋል።
በክልሉ በተለያዩ ከተሞች የተስተጋቡት መልዕክቶች መንግሥት እና ሕዝብ ለኢትዮጵያ ማንሠራራትና የከፍታ ጉዞ እጅ ለእጅ ተያይዘው መትመማቸውን በግልፅ ያሳዩ የልማት ቋንቋዎች ናቸው ነው ያሉት።
እናዳምጣለን! እናከብራለን! እንተገብራለን! ብለዋል በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየእንቅርት በሽታ ምንድን ነው?
Next articleሕዳሴ ሁሉንም ያስተሳሰረ እና አንድነትን ያጠናከረ ነው።