የኅብረት ሥራ ማኅበራት ገበያን ማረጋጋት እንዲችሉ መደገፍ እና አቅማቸውን ማሳደግ ይገባል።

7

አዲስ አበባ፡ መስከረም 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኅብረት ሥራ ማኅበራትን የገበያ ድርሻ ማሳደግ ዓላማ ያደረገ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ገበያን በማረጋጋት በኩል የተሻለ ሚና መጫዎት እንዲችሉ መደገፍ እና አቅማቸውን ማሳደግ ይገባል ብለዋል። ኮሚሽነሩ የአባላቱን ተጠቃሚነት ማረጋገጥም ሌላኛው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ እንደኾነ ጠቁመዋል።

የኅብረት ሥራ ማኅበራት አቅምን በትብብር ማሳደግ ከተቻለ የገበያ ዋጋን የሚቀበሉ ብቻ ሳይኾን የሚወሰኑ ማድረግ እንደሚቻልም ተገልጿል።
በመድረኩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ልምድ እና ተሞክሮ ቀርቧል። በግብይት ተግዳሮቶች ላይም ወይይት እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ -ከአዳማ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ የሕዳሴን ድል በሌሎች ልማቶች ለመድገም ተነስቷል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleበህዳር ወር በሚካሄደው 10ኛው የከተሞች ፎረም ከ150 በላይ ከተሞች ይሳተፋሉ።