“የድጋፍ ሰልፉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቅቋል” የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ

11

ባሕር ዳር: መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለምረቃ መብቃቱን ተከትሎ በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ.ር) አስታውቀዋል።

የድጋፍ ሰልፉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ለሚገኙ የጸጥታ እና የደኅንነት አካላት ኦረንቴሽን ተሰጥቶ ወደ ሥራ መገባቱን ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት።

የአማራ ሕዝብ ሰልፉ በሰላም እንዲካሄድ ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን ላደረገው ቀና ትብብርም አመስግነዋል።

ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ.ር) ከሰልፉ ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ሰልፉ በሰላም እንዲካሄድ እና ያለ አንዳች እንከን እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የጸጥታ እና ደኅንነት ግብረ-ኃይል እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ፣ ሚሊሻ እና ሰላም አስከባሪ አካላትም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ፈጣሪ ለዚህ ስላበቃን እናመሰግነዋለን” ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ
Next articleሕዳሴ አኩሪ ገድል የሚዘከርበት የአሸናፊነት ብራና ነው።