የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የሀገር እና ሕዝብን ጥንካሬ ያሳየ ዳግማዊ ዓደዋ ነው።

2
ደብረ ማርቆስ፡ መስከረም 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ”እምርታ እና ማንሰራራት” በሚል መሪ መልዕክት ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።
የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ከሌሎች ልማቶች ሁሉ ለየት የሚያደርገው በራስ አቅም የተሠራ መኾኑ ነው።
በውይይቱም የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ላባቸውን እና ደማቸውን የገበሩበት፤ በተባበረ ክንድ በአንድ ድምጽ የቆሙበት፤ የወል ትርክት ግንባታ ላይ ትልቅ ትርጉም የሰጠ፤ ሀገራዊ ገጽታን የገነባ፤ በኅብረት መቻልን ያረጋገጠ ፕሮጀክት እንደኾነም ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleትምህርትን በጉልበት፣ በገንዘብ እና በሃሳብ መደገፍ፦
Next articleየፌዴራል እና የጎንደር ከተማ ከፍተኛ መሪዎች በጎንደር ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው።