
አዲስ አበባ፡ መስከረም 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አካባቢዎች ለሚኖሩ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች በቤተመንግሥት ማዕድ አጋርተዋል።
የማዕድ ማጋራቱ መርሐ ግብር የተከናወነው የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ነው።
ግብዣ የተደረገላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎችም ለተሰጣቸው ክብር እና መስተንግዶ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አመሥግነዋል። ደስታቸውም ከፍ ያለ እንደኾነ ለአሚኮ ገልጸዋል።
ይህ አቅመ ደካሞችን የማሰብ፤ የመረዳት መልካም እሴት በሌሎችም እንዲሰፋ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተግባር አስተማሪ እና የሚመሠገን ነው ብለዋል።
መልካም አዲስ ዓመት!
ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!