“ነገን እጅግ የተሻለ ለማድረግ ተነሥተናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) 

2

ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጳጉሜን አምስት የነገው ቀንን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ትናንትን በመጠቀምና በማረም፣ ዛሬ ላይ ተግተን በመሥራት፣ ነገን እጅግ የተሻለ ለማድረግ ተነሥተናል፡፡ በአናሎግ ዘመን የነበሩ ችግሮች በዲጂታል ዘመን አይደገሙም፡፡ ነገ “ዲጂታል ኢትዮጵያ” ፕሮጀክት ከመሆን አልፎ ባሕል ይሆናል ብለዋል፡፡ ንግድ እና አገልግሎታችንን በማቀላጠፍ፣ መረጃዎቻችንን ተደራሽ በማድረግ፣ አንድ ሰው አንድ እንዲሆን በማስቻል፣ የፋይናንስ ሥርዓታችንን ይበልጥ ተደራሽ ቀልጣፋ እንዲሆን በማድረግ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን በየአቅጣጫው በማስፋፋት፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ እንዲሳካ የሁላችንን ጥረትና ትኩረት ይፈልጋል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተባብረን በመሥራት የትኛውንም ልማት ማሳካት እንችላለን።
Next article“ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ነገዋን እየሠራች ነው!” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት