“ኢትዮጵያ ተነሥታለች፤ ከእንግዲህ ወደኋላ አትመለስም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

14
ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጳጉሜን አራት የማንሠራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሠራራት፤ ኢትዮጵያ ተነሥታለች፡፡ ከእንግዲህ ወደኋላ አትመለስም ብለዋል።
ይሄ የማንሠራራት ጉዞዋ በዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የታገዘ መሆን አለበት፡፡ በተለይም በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በአምራችነት እና በአይሲቲ ዘርፎች የላቁ ውጤቶችን እያስመዘገብን መቀጠል አለብን፡፡ ለዕድገታችን አጋዥ የሚሆን ሀብት መፍጠር እና ገቢ መሰብሰብ ይገባናል፡፡ ዕድገታችን የሚያመነጨውን ገቢና ሀብትም በሚገባ ሰብስበንና ቆጥበን ለብልጽግና ግባችን መጠቀም አለብን፡፡ የጀመርነውን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በማሣለጥና በማሳካት የኢትዮጵያ ማንሠራራት ወደ ዘላቂ የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲለወጥ እናደርጋለን ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየታሪክና ፖለቲካ ብያኔን የለወጥንበት የጋራ ችሎታችን ትዕምርት ነው!
Next articleከተባበርን በርካታ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ልማቶችን መሥራት እንችላለን።