
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዛሬ ጠዋት በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ መክፈቻ መርሐ ግብር አፍሪካ የአየር ንብረት ተጠቂ ብቻ ሳትኾን የመፍትሄውም አኅጉር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተው በመግለፅ ከፍተዋል።
እንደ አረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ ሥራ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃ የተመቸ ግብርና እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በማንሳትም የኢትዮጵያን ሥራዎች በምሳሌነት በማንሳት አውስተዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከአየር ንብረት እርዳታ ወደ አየር ንብረት ኢንቨስትመንት ለውጥ ሊደረግ እንደሚገባ በመግለጽ Climate Innovation Compact የተሠኘ በ2030 1 ሺህ አፍሪካ መር መፍትሔዎች የሚገኙበትን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።
አፍሪካ በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ዋስትና እና የሥነ ምኅዳር ጥበቃ የመምራት አቅሟንም በማጽናት አንስተዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2027 የCOP32 ጉባኤን ለማስተናገድ ያላትን ጥያቄም አቅርበዋል። ይኽም ሀገራችንን እና አኅጉራችንን በአየር ንብረት ጥበቃ ተግባር የመሪነት ሚና የሚያጎናፅፍ ይኾናል ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!