የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልድያ ዲስትሪክት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።

2
ወልድያ: ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልድያ ዲስትሪክት የዘመን መለወጫ በዓልን አስምልክቶ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልድያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሽመልስ ያረጋል ባንኩ ከፋይናንስ ዘርፍ አገልግሎቱ ባሻገር ማኅበራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደኾነ ተናግረዋል።
ባንኩ 1 ሚሊዮን 229 ሺህ ብር ወጭ በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 215 ወገኖች የምግብ ዱቄት፣ ዘይት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኀላፊ ሞገስ ሞላ ባንኩ ለከተማው ሕዝብ ለሚሰጠው ማኅበራዊ አገልግሎት አመስግነዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም አዲስ ዓመትን በደስታ እንድንቀበል ለተደረገልን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የጽናት ቀን” በወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተከበረ።
Next articleጽናት ለፀጥታ ተቋማት የአሸናፊነት ኃይል ነው።