ለሀገራችን ሁለንተናዊ ሰላም በጽናት ዘብ እንቆማለን።

1
ደሴ: ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ ጷጉሜን 1 የጽናት ቀን በተለያዩ ወታደራዊ የሰልፍ ትርዒቶች “ጽኑ መሠረት፣ ብርቱ ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት ታስቧል።
በሰልፍ ትርዒቱ የታደሙት የፀጥታ ኃይሎች የጽናት ቀንን ስናከብር እና ለዚህ እንድንበቃ የኾነው በጽናት ለሀገራቸው ዘብ የቆሙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ሌሎች የፀጥታ አባላት በሚከፍሉት መሰዋትነት ነው ብለዋል።
በቀጣይም “ለሁለንተናዊ ሰላማችን በጽናት ለሀገራችን ዘብ እንቆማለን” ነው ያሉት።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሰይድ ዓሊ በጽናት የከተማችን እና የሕዝባችንን ሰላም ጠብቀናል ብለዋል።
በቀጣይም የፀጥታ መዋቅሩ ለአስተማማኝ ሰላም ተግቶ በጽናት እደሚሠራ ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ፊኒክስ ሀየሎም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የጽናት ቀን” በባሕር ዳር ከተማ እየተከበረ ነው።
Next article“የማኅበሩ ዓላማ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው”