
አዲስ አበባ: ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፈጣን፣ ተለዋዋጭ፣ የሃሳብ የበላይነት፣ ፈጠራ እና ብቃት ለሚጠይቀው ዘመን ብቁ እና ተወዳዳሪ ባለሙያ እና መሪ መፍጠር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የአጫጭር ሥልጠና፣ የምርምር እና የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ነው። ተቋሙ የበርካታ ተቋማትን የቴክኒካል ብቃት ማዕቀፍን ሠርቷል፤ እየሠራም ይገኛል።
ባለፋት ዓመታት በርካታ የሥራ መሪዎችን እና ባለሙያዎችን አጫጭር የሥልጠና አገልግሎትም ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ደሳለኝ ጣሰው በቢሾፍቱ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሥራ አመራር የሥልጠና ማዕከል ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ዋና ሥራ አሥፈጻሚው ከሠራተኞች ጋር በነበራቸው ውይይት ፈጣን፣ ተለዋዋጭ፣ የሃሳብ የበላይነትን፣ ፈጠራ እና ብቃት ለሚጠይቀው ዘመን ብቁ እና ተወዳዳሪ ባለሙያ እና መሪ መፍጠር ይገባል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው የቢሾፍቱ የሥራ አመራር ማዕከል ነባር ተቋም ነው ያሉት ሥራ አስፈጻሚው ተቋሙን በቴክኖሎጅ እና በሌሎች መስኮች የበለጠ ማዘመን እንደሚገባም ሥራ አሥፈጻሚው ገልጸዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን ዳረጎት
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!