
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የጽናትን ቀን አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን የምታረጋግጠው መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ነው ብለዋል።
በሁሉም ዘርፎች በምናደርገው ተጋድሎ የኢትዮጵያን መሠረት እናጸናለን፡፡ ለማናቸውም ችግሮች የማትበገር፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል የምትቀይር፣ በመጪው ዘመንም ከዓለም ኃያላን ተርታ የምትሰለፍ ብርቱ ሀገር በደምና በላብ እንገነባለን ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!