
ባሕር ዳር: ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል በመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዓሉን አስመልክተው በኤክ ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የትሩፋት እንዲኾን ከልብ እመኛለሁ ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!