
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለመውለድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት እንኳን ለ1500ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።
መውሊድ የሠላም እና የአብሮነት በዓል ነው። ወንድማማችነት እና መተሳሰብ የሚያንፀባርቅበት በመሆኑ ማኅበራዊ ግንኙነት እና የርስበርስ ትስስርን ለማጠናከር የላቀ ሚና አለው ነው ያሉት።
በዓሉ የትውልድ ስብዕና የሚታነጽበት፣ ደግነትና ዘመን ተሻጋሪ መልካም ሥራዎች የምናስታውስበት ነው ብለዋል። የታላላቆችን መልካም ሥራ ከማሰብ በተጨማሪ ለሀገር ሰላም እና ለሕዝቦች አንድነት በጋራ በመትጋት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት በመልእክታቸው።
ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ለሀገራዊ አንድነት በጋራ የሚቆምበት፤ የበዓሉ መገለጫ የሆኑት የመረዳዳትና የመደጋገፍ እሴቶች ይበልጥ የሚጠናከሩበት በዓል እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።
መልካም የመውሊድ በዓል እንዲኾንም ተመኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን