
አዲስ አበባ: ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጳጉሜ 4 የማንሠራራት ቀን “ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሠራራት” በሚል መሪ መልዕክት ይከበራል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) 2017 ኢትዮጵያ በርካታ ስኬቶች ያስመዘገበችበት፣ በዓለም አደባባይ ያንሰራራችበት ዓመት በመኾኑ ጳጉሟ 4 የማንሠራራት ቀን በሚል ይከበራልም ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የጀመረቻቸውን ፕሮጀክቶች ያጠናቀቀችበት እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የጀመረችበት ነው ሲሉም አንስተዋል።
ይህ ዓመት ደግሞ የኢትዮጵያን መዳረሻ የምናይበት ስኬቶቻችን የምንዳስስበት ይኾናልም ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በአየር መንገድ፣ በማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና ከወደብ ጋር የሚያገናኙ ግዙፍ መንገዶችን ለማገንባት ዝግጅት ላይ መኾኗን ያነሱት ሚኒስትሩ ይህ ደግሞ አንዱ የኢትዮጵያን ማንሠራራት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን