ጳጉሜን 3 የዕምርታ ቀን በሚል ይከበራል።

12
አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም የዕምርታ ቀን በሚል እንደሚከበር የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) ገልጸዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ በዚህ ቀን ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ድሎች የሚታሰቡበት ቀን ነው።
በዚህ ዕለት ባለፉት ዓመታት በግብርና እና በኢንዱስትሪ የተሠሩ ሥራዎች የሚታወሱበት ቀን እንደሚኾንም ነው ዶክተር ለገሰ ቱሉ ያብራሩት።
በተለይም በግብርና ልማት ሥራዎች እንደ ሀገር የተገኙ ስኬቶች ይወሱበታልም ነው ያሉት።
በዚህ ዕለት በአረንጓዴ መርሐ ግብር የተገኙ ድሎችም እንደሚነሱበት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
በዚህ ዕለት በተኪ ምርት የተሠሩ ሥራዎች ይፋ ከመደረጋቸው በተጨማሪ የማዕድን ዘርፉ ዕድገትም ይዳሰስበታል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“ጳጉሜ 2 ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር መሠረት የሚጣልበት ቀን ይኾናል” ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር)
Next articleኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ያንሠራራችበት ዓመት በመኾኑ ጳጉሜ 4 የማንሠራራት ቀን በሚል ይከበራል።