
አዲስ አበባ: ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጳጉሜ 2 የኅብር ቀን “ብዝኀን የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ መልዕክት ይከበራል ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በዚህ እለት የኅብረ ብሔራዊ አንድነት የኾኑ ድሎቻችን ይታወሳሉ ብለዋል። እንደ ሀገር የተከናወኑ ትላላቅ እሴቶች እንደሚታወሱም አንስተዋል።
ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር መሠረት የሚጣልበት እለት ይኾናልም ነው ያሉት።
በዚህ እለት በየአካባቢው የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችም ለዓለም ይተዋወቃሉ ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን