
አዲስ አበባ: ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ቀጣዮች የጳግሜ ቀናት አከባበርን አስመልክቶ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን አንስተዋል።
በ2017 ዓ.ም ኢትዮጵያ በበርካታ ችግሮች ተፈትና ወደ እምርታ የተሸጋገረችበት ነው ብለዋል።
ጳጉሜ ደግሞ ያለፈውን ዓመት የምንሸጋገርበት ድልድይ እና ዝግጅት የሚደረግበት ነው ብለዋል።
እነዚህ ቀናት ጉድለቶቻችን የምንገመግምበት፣ ለቀጣይ የምንዘጋጅበት ነው ብለዋል።
የጳጉሜ ቀናትን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ስያሜዎች እንደሚከበሩ ሚኒስትሩ አንስተዋል።
ጳጉሜ 1 የጽናት ቀን በሚል ይከበራል ያሉት ሚኒስትሩ በዚህ ዕለት ብዙ የሠሩ ሠዎች የሚመሠገኑበት ነውም ሲሉ ተናግረዋል። ጳጉሜ 1 የጽናት ቀን በሚል “ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር” በሚል መሪ መልዕክትም ይከበራል። ይህ ቀን ችግሮቻችንን በጽናት በመቆም አስደናቂ ድሎች ለማስመዝገብ ቃል የምንገባበት ነውም ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን