የብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ያሠለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች አስመረቀ።

55
ባሕር ዳር: ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብር ሸለቆ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ያሠለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሥልጠና ዋና መምሪያ ኀላፊ ሌተናል ጀኔራል ይመር መኮንንን ጨምሮ ሌሎችም ጄኔራል መኮንኖች ተገኝተዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሥልጠና ዋና መምሪያ ኀላፊ ሌተናል ጀኔራል ይመር መኮንን የኢትዮጵያን የውጭ ጠላቶች እና የውስጥ ባንዳዎችን ፍላጎት ጠንቅቆ በመረዳት አንድነታችንን አረጋግጠን ሀገራችንን ወደፊት ማራመድ ይኖርብናል ብለዋል። ተመራቂ ወታደሮች ከየትኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ ወገንተኝነት ነጻ ኾነው ሕዝባቸውን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል። ከማንኛውም የጎሳም ይሁን የሃይማኖት ተጽእኖ በመላቀቅ ሕዝብ እና ሀገር የጣለባቸውን ኀላፊነት መወጣት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።
የተቋሙን መርሕ በመከተል የዘመናዊ ሠራዊት ባሕሪን በመላበስ ለሠራዊቱ ተጨማሪ አቅም መኾን እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል። ለሀገር ትልቅ አቅም በመኾን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በጀግንነት መወጣት እንደሚገባቸውም ተናግረዋል። የታላቁ የሕዳሴ ግድብ በምረቃ ዝግጅት እና በአዲስ ዋዜማ የተካሄደ ምርቃት በመኾኑ የተለየ ነው ብለዋል። ተመራቂዎች የመሠረታዊ ውትድርና የሚያስፈለገውን ሥልጠና ወስዳችሁ የጀግናው መከላከያ ሠራዊት አባል በመኾናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleመሃይምነትን ማንም መደገፍ የለበትም፤ የትምህርት ጉዳይ ለድርድር መቅረብም የለበትም።
Next articleመንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ሕዝብን ለመካስ ቁርጠኛ መኾናቸውን የቀድሞ ታጣቂዎች ተናገሩ።