የጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል ወታደሮችን እያስመረቀ ነው።

32
ባሕር ዳር: ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች እያስመረቀ ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ ለ11ኛ ዙር በመሠረታዊ ውትድርና ሙያ ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች እያስመረቀ ነው፡፡ዛሬ ለምረቃ የበቁት የሠራዊት አባላት የተሟላ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ያጠናቀቁ መኾናቸው ተመላክቷል፡፡በትምህርት ቤቱ በነበራቸው ቆይታ በቀጣይ ማንኛውንም የግዳጅ ተልዕኮ በብቃት መወጣት የሚያስችል የንድፈ ሃሳብ፣ የክህሎት እና የተግባር ስልጠና ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ፈቱ።
Next articleየሁርሶ ማሰልጠኛ ማዕከል ምልምል ወታደሮችን እያስመረቀ ነው።