የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖን አስጀመሩ።

6
አዲስ አበባ: ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖን በአዲስ አበባ ከተማ አስጀምረዋል። ኤክስፖው ከነሐሴ 24 እስከ ነሐሴ 29 /2017 ዓ.ም ድረስ በጥራት መንደር እንደሚካሄድ ተገልጿል። 168 አምራቾች፣ ጅምላ አከፋፋዮች፣ አገልግሎት ሰጭዎች፣ አስመጭ እና ላኪዎች፣ ክልሎች እና የከተማ አሥተዳደሮች በኤክስፖው ተሳታፊ ናቸው።
የንግድ ሳምንት ኤክስፖው የሀገር ውስጥ ምርቶችን ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ የተገለጸ ሲኾን ምርቶች በቅናሽ ዋጋ የሚሸጡበት እና የሚሸመቱበት ነውም ተብሏል።
ዘጋቢ፦ ኢብራሒም ሙሐመድ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleብቁ ዜጎችን ማፍራት የ25 ዓመታቱ የአሻጋሪ እና የዘላቂ ልማት ዕቅዱ የትኩረት አቅጣጫ ነው።
Next articleየመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ፈቱ።