
ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን መርሐቤቴ ወረዳ የገረን እና የአፈዘዝ ቀበሌዎች ላይ በተሳሳተ ዓላማ ወደ ጫካ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 67 የታጠቁ ኃይሎች ሰላምን መርጠዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ አለማየሁ ባለፍት ጊዜያት የተጀመረው በሰላም ታጣቂዎችን የመመለስ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። ዋና አሥተዳዳሪው ከዚህ አንጻር የመርሐቤቴ ወረዳ ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል ።
የታጣቂዎች በሰላም መግባት በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሚናው የጎላ እንደኾነ ገልጸዋል። ይህ ውጤት መንግሥት ለሰላም በሰጠው ትልቅ ዋጋ እና ሕዝቡ ለሰላም የሰጠው አወንታዊ ምላሸ እንደኾነ ነው የተናገሩት። በሁሉም አካባቢዎችም ይህን ከመገዳደል የተሻለ ተሞክሮው ሊቀስሙ እንደሚገባ አንስተዋል።
ዋና አሥተዳዳሪው በአንድ አካባቢ የሚወሰደው የሰላም እርምጃ ለሌላውም አካባቢ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መኾኑን ገልጸዋል። አሁን እየታየ ያለው በጎ እርምጃ እንዲሰፋም ጠንክረን እንሠራለን ነው ያሉት።
ለመጣው ውጤት መከላከያ ሠራዊት፣ የወረዳው መሪዎች እና የወረዳው ሕዝብ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!