
ባሕር ዳር: ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በማጠቃለያ ዝግጅቱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የርእሰ መሥተዳድሩ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪና የአሚኮ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። አሚኮ በ30 ዓመታት ጉዞው ለሀገር ሰላም፣ ዕድገት፣ ለሕዝብ አንድነት እና ለኢትዮጵያ ክብር ሠርቷል። አሚኮ በሠራቸው ታላላቅ ሥራዎች በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከኾኑ ሚዲያዎች አንደኛው ነው። ላደረገው አበርክቶም በሀገር አቀፍ እና በክልሉ ዕውቅና የተሰጠው ታላቅ ሚዲያ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!